የጠዳ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ለ17ኛ ጊዜ በአምስት የጤና ሙያ ዘርፎች ያሠለጠናቸውን 572 ተማሪዎች አስመረቀ!!!
የጠዳ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ለ17ኛ ጊዜ በአምስት የጤና ሙያ ዘርፎች ያሠለጠናቸውን 572 ተማሪዎች አስመረቀ!!!
በምርቃት ስነ-ስርዓቱም ከጤና ሚኒስቴር፣ከክልል፣ከዞን ና ጎንደር ከተማ አስተዳደር በርካታ አመራሮች ና እንግዶች የተገኙ ሲሆን የኮሌጁ ዲን አቶ ዘመነ ሀብቱ ባደረጉት የመግቢያ ንግግር ኮሌጁ በትምህርት ና ስልጠና ፣በችግር ፈች የምርምር ስራዎች ና የማህበረሠብ አገልግሎት አርአያነት ያለው ስራ እየሠራ መሆኑን አውስተው ህዝቡን በተሻለ አቅም ለማገልገል ዲግሪ ና ከዚያ በላይ ፕሮግራሞችን ለመጀመር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል!!!
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ዘውዱ ማለደ ለተማሪዎች የስራ መመሪያ በሠጡበት ወቅት እንዳሉት ኮሌጁ ከሌሎች አቻ ኮሌጆች ብልጫን እየወሠደ ና ከፍተኛ ለውጥ ላይ ያለ መሆኑን ጠቅሠው ኮሌጁ ወደ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅነት ለማደግ የሚያደርገውን ጥረት ከተማ አስተዳደሩ ሙሉ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ የሠው ሃብት ልማት ና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳኛቸው ዳሬ በበኩላቸው ጠዳ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በማህበረሠብ አገልግሎት ና ችግር ፈች የምርምር ስራዎች ቀዳሚ ኮሌጅ ነው ብለዋል!!!
የጤና ሚኒስቴር ተወካዩ አቶ ታጀበ ኩመላ የኮሌጁን እንቅስቃሴዎች አድንቀው ሚኒስቴር መ/ቤቱ ለኮሌጁ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የኮሌጁ የአካዳሚክ ና ምርምር ጉዳዮች ምክትል ዲን አቶ አስናቀው አስረስን ጨምሮ የተለያዩ የኮሌጁ የስራ ኃላፊዎች ና የጠዳ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ የተማሪዎች ህብረት የህዝብግንኙነት ኃላፊ ተማሪ ቅድስት ውብሸት በመድረኩ የእንኳን ደስአላችሁ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል!!!