የጠዳ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በጤና ኤክስቴንሽን የብቃት ምዘና ሪከርድ አስመዘገበ!!!
በጠዳ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ የጤና ኤክስቴንሽን የብቃት ምዘና የማለፍ ምጣኔ ሪከርድ ተመዘገበ!!!( ከዘመነ ሐብቱ -የተላለፈ መልዕክት)
በበርካታ ጥረቶችም ጭምር የማይሣካውና አስቸጋሪው የጤና ኤክስቴንሽን የብቃት ምዘና (CoC) የማለፍ ምጣኔ በመጀመሪያ ዙር (first shot) ብቻ በጠዳ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ 88% የማለፍ ምጣኔ እውን በመሆን ትልቅ ሪከርድ ተመዝግቧል!!!
ይህ ውጤት ከስታንዳርዱ 85%ም በላይ ነው!!!
ይህ ትልቅ ውጤት ሊመጣ የቻለው የኮሌጁ መምህራንና የሠርቶማሣያ ባለሙያዎች ወርክሾፕ አዘጋጅተው ተማሪዎችን በማዘጋጀታቸውና በጎንደር ዞኖች የሚገኙ የጤና ተቋማት በርካታ ድጋፎችን በማድረጋቸው፣ ጤና ቢሮ እና ጃፓይጎ ኢትዮጵያ ተከታታይ ድጋፎችን በማድረጉ ፣የጎንደር ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ክላስተር የተሻለ ክትትል ስላደረገ እንዲሁም የኮሌጃችን ማኔጅመንት ፣አካዳሚክ ኮሚሽንና የአስተዳደር ሠራተኞች በቅንጅት ተናበው በመስራታቸው በመሆኑ ሁሉንም ድጋፍ ያደረጉ አካላት በጣም እያመሠገንኩ በቀጣይ በሚኖሩ ምዘናዎች አሁን የተገኘውን ውጤት መነሻ (benchmark) በማድረግ ከፍ ላለ ውጤት የምንተጋ መሆናችንን ማረጋገጥ እፈልጋለሁ!!!
ዘመነ ሐብቱ- የጠዳ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ዲን
ጥቅምት 19 ቀን 2015 ዓ.ም
ጎንደር