የጠዳ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ለ17ኛ ጊዜ በአምስት የጤና ሙያ ዘርፎች ያሠለጠናቸውን 572 ተማሪዎች አስመረቀ!!! በምርቃት ስነ-ስርዓቱም ከጤና ሚኒስቴር፣ከክልል፣ከዞን ና ጎንደር ከተማ አስተዳደር በርካታ አመራሮች ና እንግዶች የተገኙ ሲሆን የኮሌጁ ዲን አቶ ዘመነ ሀብቱ ባደረጉት የመግቢያ ንግግር ኮሌጁ በትምህርት ና ስልጠና …
በቅርቡ ለጠዳ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ 10 ማይክሮስኮፖችን ኮሌጁ ድረስ በማምጣት ድጋፍ ያደረገው ኬሞኒክስ ኢንተርናሽናል (GHSC-PSM) ዛሬም በድጋሚ 6 አዳዲስና ደረጃቸውን የጠበቁ ተጨማሪ ማይክሮስኮፖችን ድጋፍ ስላደረገልን በጣም እናመሠግናለን!!!
በጠዳ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ የጤና ኤክስቴንሽን የብቃት ምዘና የማለፍ ምጣኔ ሪከርድ ተመዘገበ!!!( ከዘመነ ሐብቱ -የተላለፈ መልዕክት) በበርካታ ጥረቶችም ጭምር የማይሣካውና አስቸጋሪው የጤና ኤክስቴንሽን የብቃት ምዘና (CoC) የማለፍ ምጣኔ በመጀመሪያ ዙር (first shot) ብቻ በጠዳ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ 88% የማለፍ ምጣኔ …
የጠዳ ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ግቢውን አረንጓዴ የማድረግ ተግባርና በ2013 ተጀምሮ በ2014 ዓ.ም የተጠናቀቁ ሁለት ባለ12 የመማሪያ ክፍል ብሎኮች !!!
ከኢትዮጵያ ክልላዊ ጤና ሳይንስ ኮሌጆች ከጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጋር ብቻ በአጋርነት የሚሰራው ጃፓይጎ ኢትዮጵያ የተሰኘው ግብረሠናይ ድርጅት ላለፉት 4 ቀናት 20 ለሚሆኑ የኮሌጁ መምህራን ሲሰጥ የሰነበተው የአካዳሚክ ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል።